የአትራፊ ሶሉሽን (ACE) ሞዴልን ለማስተዋወቅ እና ለደንበኞች መረጃ ለመስጠት አፊሊየት ሆነው የሚሰሩ ግለሰቦች ሊከተሏቸው የሚገቡ ህግጋቶች፣ደንቦች ዝርዝር እና የስራ ስምምነት ውል

የአትራፊ ሶሉሽን (ACE) ሞዴል አፊሊየት ማለት በአትራፊ ሶሉሽን ፋይናንስ እና ሀውሲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ዕውቅና የተሰጣቸው ግለሰቦች የአትራፊ መኪና እቁብ ተመዝጋቢ ሆነው አልያም ሳይመዘገቡ ሞዴሉን በአግባቡ ተረድተው በዙሪያቸው ለቤተሰቦቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለስራ ባልደረቦቻቸው ወይም በተለያየ መንገድ አዲስ በሚፈጥሩት ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ለሚያገኙዋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በቃልና በተለያዩ መንገዶች ባሉበት ቦታ ሆነው መረጃ በመስጠት መኪና ፈላጊዎችን የሞዴሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

አፊሊየት ሊንክ ማለት አፊሊየት ሆነው ለመስራት የተመዘገቡ ግለሰቦች ልዩ እና ብቸኛ መለያ እንዲሆን የሚሰጥ ኮድ ማለት ነው፡፡

  • አፊሊየቶች ለደንበኞች ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለሞዴሉ ማብራሪያ ይሰጣሉ፣የስልክ ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋሉ፣ጥያቄዎችን ይመልሳሉ እንዲሁም በራሳቸው አፊሊየት ሊንክ ደንበኞች እንዲመዘገቡ ያደርጋሉ፡፡
  • አፊሊየቶች ስለ ድርጅቱም ሆነ ስለ አትራፊ የመኪና እቁብ ሞዴል ለደንበኞች መረጃ ሲሰጡ በራሳቸው ስም እንጂ በአትራፊ ሶልዩሽን ስም መሆን የለበትም፡፡
  • አፊሊየቶች የአትራፊ ሶልዩሽን ቢሮዎች በሚገኙባቸው ህንፃቸው እና አካባቢው ቢያንስ በ 500 ሜትር ክልል ውስጥ መሰብሰብ የለባቸውም፡፡
  • አፊሊየቶች የክፍያ ጊዜ ሲቃረብ ያስመዘገቧቸውን ሰዎች የስም ዝርዝር የሚያሳየውን ዳሽቦርድ ለአትራፊ ሶልዩሽን የአፊሊየት ቡድን በቴሌግራም መላክ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ለአፊሊየቶች ክፍያ የሚፈፀመው የሚጠበቅባቸውን ቅድመ-ክፍያ ፈፅመው በተመዘገቡ ተመዝጋቢዎች መጠን ተባዝቶ ነው፡፡
  • የትኛውም የማጭበርበር ሙከራ እና የስነ-ምግባር ጉድለት የውል መቋረጥ ያስከትላል፡፡

በተጨማሪም ሁሉም አፊሊየቶች ለሚቀበሉት ክፍያ የቫት ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ደረሰኝ የማያቀርቡ ከሆነ በህጉ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡